ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል አድርጓል

አዲስ አበባ ፤ ጥር 28/2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲስ ግደይ እና ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ሁለተኛ  ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም