የፌዴራል ፖሊስ ስዋት የዓለም አቀፍ ፈጣን ምላሽ መሰናክል ውድድርን በብቃት አጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል ፖሊስ ስዋት የዓለም አቀፍ ፈጣን ምላሽ መሰናክል ውድድርን በብቃት አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፦በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተዘጋጀው የ2025 የፈጣን ምላሽ መሰናክል ውድድር ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ስዋት ቡድን ውድድሩን በብቃት አጠናቋል፡፡
በውድድሩ የኩዌቱን ናሽናል ጋርድ ቡድን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ቡድንን ፤የራክ ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ቡድንን እንዲሁም የልዩ ደህንነት ሃይል ፈጣን ምላሽ ቡድኖችን በመብለጥ በብቃት ማጠናቀቁን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።