ቀጥታ፡

ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ)፡- ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ነው።


 

በመድረኩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሰብስብ አባፊራን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በምክክር መድረኩ ለጋራ ትርክት ግንባታ እና ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮሩ መነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም