ቀጥታ፡

የዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታው ዘርፉን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማጎልበት ያግዛል - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታ የግብርናውን እሴት ሰንሰለት በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በግብርና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና ጌትስ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታው በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2025 እስከ 2032 የሚተገበር ነው።

ፍኖተ ካርታው የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

May be an image of text that says 'Gates Foundation Ethiopian EthlopianATI ATI bontutuke HEPRA DAR DIGITAL AGRICULTURE ROADMAP -**--2025-2032----- Launch of the Digital Agriculture Roadmap (DAR) February 04, 2025 Addis Ababa, Ethiopia'

ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እንዳሉት የዲጂታል ግብርና ፍኖተ ካርታ ዘርፉን ለማዘመን እና ገበያ ተኮር እንዲሆን ለማስቻል ያግዛል።

የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን በስማርት ስልኮች ለአርሶና አርብቶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

የግብርናው መረጃዎችን በአንድ ቋት ለመያዝና ለማዘመን፣ የግብርና ግብዓትን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ብድርና ኢንሹራንስን ጨምሮ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

May be an image of lighting, table and dais

ከምርት እስከ ገበያ ባለው የእሴት ሰንሰለት የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት በማጎልበት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝም እንዲሁ።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ከሚሰራባቸው ዘርፎች መካከል የዲጂታል ግብርና አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል።

May be an image of 1 person, television, newsroom and text

በዚህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዘርፉን በማዘመን ይገጥሙ የነበሩ ተግዳሮቶች ለመፍታት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው አመልክተዋል።

ዲጂታል ግብርና በትክክለኛ የመረጃ ትንተና ላይ የተመሰረተ ፈጣን ውሳኔ በመስጠት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ያግዛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ትክክለኛ መረጃዎችን ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ በማድረስ በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የዲጂታል ግብርና አስፈላጊ እንደሆነም ገልጸዋል።

May be an image of 1 person

አርሶ እና አርብቶ አደሩ ከማምረት እስከ ገበያ ባለው እሴት ሰንሰለት መረጃ ባለማግኘቱ ይፈጠሩ የነበሩትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በጌትስ ፋውንዴሽን የግብርና ልማት ምክትል ዳይሬክተር ኦቢያ ከኸሊፋ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ የግብርናን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ ላይ በጋራ እየሰሩ ያሉትን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

May be an image of 1 person, television, dais, newsroom and text that says 'FANA KAA DI'

የግብርናው ዘርፍ ለመኖር ብቻ ሳይሆን የብልጽግና እና የእደገት መሰረት በመሆኑን ጠቁመዋል።

በዲጂታል ግብርና ላይ ቀደም ተብሎ በኢትዮጵያ የተጀመሩ ሥራዎች በመኖራቸው አሁን በአንድ ላይ ለመስራት መሰረት የሚጥሉና የተጀመሩ ሥራዎች የሚደነቁ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም