በዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ የግሉን ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ነገ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
በዘላቂ ሰላም ግንባታ ላይ የግሉን ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ጥር 27/2017(ኢዜአ)፦ በሀገር ዘላቂ ሰላም ግንባታ ዙሪያ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ተሳትፎ እና ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የሰላም ሚኒስቴር ገለፀ።
የምክክር መድረኩ የሰላም ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሴንተር ፎር ኢንተርናሽናል ፕራይቬት ኢንተርፕራይዝ ጋር በመሆን የተዘጋጀ ነው።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ቀነኒሳ ለሚ(ዶ/ር) በጋራ መግለጫ በሰጡት መግለጫ የምክክር መድረኩ "የግሉ ዘርፍ ሚና በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ግንባታ" በሚል መሪ ሀሳብ በአድዋ ድል መታሰቢያ ነገ ይካሄዳል።
በመድረኩ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ተመላክቷል።

የንግዱ ማህበረሰብን ጨምሮ የግሉ ዘርፍ በሀገር ዘላቂ ሰላም ግንባታ ተግባራት ላይ ተሳትፎና ሚናውን ለለማጠናከር ያለመ መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።
ለህብረ ብሄራዊ አንድነት፣ ለአብሮነትና ለጋራ ትርክት ግንባታ የንግዱ ማህበረሰብ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን ተገልጽል።
የጋራ ቤታችን በመምከር ከግሉ ዘርፍ ምን ይጠበቃል በሚለው ላይ የጋራ በማድረግ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የንግዱ ማህበረሰብ የሰላም እና የሀገር ግንባታ እና ተያያዠ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡም ተመላክቷል።