የመሪዎች ጉባዔውን ካለፉት ጊዜያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል- አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የመሪዎች ጉባዔውን ካለፉት ጊዜያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል- አዚዛ ገለታ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2017 (ኢዜአ)፦38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ካለፉት ጊዜያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) ገለጹ።
የጉባዔው ተሳታፊ አገራት ቀዳሚ ልዑካን ቡድን የመሪዎች ጉባዔ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ጎብኝተዋል።
የቡድኑ አባላት ብሔራዊ ቤተመንግሥት፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክብር ሳሎን ፣አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር እና የአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤትን ተመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አዚዛ ገለታ (ዶ/ር) ጉብኝቱ ጉባኤው ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለው ዝግጅት ተሳታፊ አገራት በቂ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
ለዘንድሮው የሕብረቱ ጉባኤ ኢትዮጵያ በላቀ ደረጃ ዝግጅት በማድረግ የተሳካ መስተንግዶ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ እንግዶች ኢትዮጵያ ስኬታማ ጉባኤን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን እንደተገነዘቡ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።