ቀጥታ፡

ኢዜአ በዲጂታል አማራጭ የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመረው ስራ የአህጉሪቷን ጥቅሞች በጋራ ለማስጠበቅ ያግዛል -ፒተር ላም ቦዝ

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2017(ኢዜአ)፦ኢዜአ በዲጂታል አማራጭ የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመረው ስራ የአህጉሪቷን ጥቅሞች በጋራ ለማስጠበቅ እንደሚያግዝ የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ንቅናቄ (SPLM) ዋና ጸሃፊ ፒተር ላም ቦዝ ገለጹ።

የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ንቅናቄ (SPLM) ዋና ጸሃፊ ፒተር ላም ቦዝ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ ሰሞኑን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

ዋና ጸሃፊው በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አዲሱን የሚዲያ ኮምፕሌክስና የዲጂታል ሚዲያ መሰረተ ልማት ጎብኝተዋል።


 

ዋና ጸሃፊ ፒተር ላም ቦዝ በዚሁ ወቅት አፍሪካን አቅሞች ለማስተሳሰርና የጋራ ትርክት ለመፍጠር ጠንካራ አፍሪካዊ ሚዲያ ሊኖር እንደሚገባም ተናግረዋል።

ከዚህ አኳያ ኢዜአ በዲጂታል አማራጭ የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን “pulse of Africa’’ በሚል ስያሜ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ተደራሽ ለመሆን የጀመራቸው ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም አህጉሪቷ በልማትና በሌሎችም መስኮች ያላትን እምቅ አቅም ለማስተዋወቅ ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል ብለዋል።


 

ከአፍሪካ ውጭ ያሉ መገናኛ ብዙሃን የአፍሪካዊያንን እውነት በማስተዋወቅ ረገድ ውስንነት እንደነበራቸው በመጥቀስ፤ ኢዜአ በዲጂታል አማራጭ የአፍሪካ ድምጽ ለመሆን የጀመረው ስራ አህጉሪቷን በሚገባት ልክ ለማስተዋወቅ ያግዛል ብለዋል።

ዋና ጸሃፊ ፒተር ላም ቦዝ፤ የኢዜአ ሚዲያ ኮምፕሌክስ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደራጀቱን አድንቀው፤ ኢዜአ የአፍሪካ ሁነኛ ድምጽ ለመሆን በዲጂታል አማራጭ የጀመረውን ጉዞ ሁሉም አፍሪካዊ ሊደግፈው ይገባል ብለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም