ቀጥታ፡

ሃገራዊ የብልጽግና ጉዞን ለማፋጠን በጉባኤው የተቀመጡትን አቅጣጫዎች በቁርጠኝነት መፈጸም ይገባል - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፤ ጥር 26/2017(ኢዜአ)፦ በጉባዔው የተቀመጡትን አቅጣጫዎች በውጤታማነት በመፈፀም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ጉዞ ለማፋጠን በቁርጠኝነት መስራት አንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ አሳሰቡ።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ መካሄዱ ይታወቃል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ በድምቀትና ዓላማውን ባሳካ መልኩ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ለፓርቲያችንም ሆነ ለሀገራችን በሚመጥን ከፍ ያለ ደረጃ የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ አካላት በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ጉባዔው በአንደኛው የፓርቲው መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈፃፀም በጥልቀት የተገመገሙበት፣ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የተሻሻለበት፣ በአሰራሩ መሰረት ነፃ፣ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ የአመራር አካላት የተመረጠበት መሆኑንም አንስተዋል።

በጉባዔው የተቀመጡትን አቅጣጫዎች በውጤታማነት በመፈፀም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ጉዞ እንድናፋጥን ሁላችንም በቁርጠኝነት እንድንሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ" ሲሉ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም