የታንዛኒያው ቻማ ቻማ ፑንዱዚ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢማኑኤል ቺምቢ መልዕክቶች - ኢዜአ አማርኛ
የታንዛኒያው ቻማ ቻማ ፑንዱዚ ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢማኑኤል ቺምቢ መልዕክቶች
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል የአመራር ጥበብ ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ እና ታንዛንያ ለጋራ ልማትና ብልጽግና ትብብራቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።
የሀገራቱ የረጅም ጊዜ ግንኙነት በፓርቲ ለፓርቲ ትብብርም ተጠናክሮ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
አፍሪካን ከተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ለማውጣት አህጉር አቀፍ ትብብርን ማጎልበት ይገባል።
ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ ሆና ያከናወነቻቸው ሁለንተናዊ የልማት ስራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶች የሚደነቁ ናቸው።