ቀጥታ፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመምሪያውን ፕሮጀክቶች ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017 (ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ  ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። 

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የተገነባውን ዘመናዊ የብሎኬት እና የቴራዞ ማምረቻ ፋብሪካን ተመልክተዋል።

ማምረቻ ፋብሪካው ባለ20 ባለ15 እና ባለ10 ሃያ ሺህ ብሎኬት በቀን ማምረት የሚችል ከመሆኑም በላይ ክላስ ኤ፣ ክላስ ቢ እና ክላስ ሲ የተሰኙ ብሎኬቶችን እንደሚያመርት እና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል። 

በተጨማሪም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በመምሪያው እየተገነባ ያለውን የባህር ኃይል መምሪያ ቢሮ ህንጻ እና ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠርን አላማ ያደረገ የአረንጓዴ ልማት ስራም ተመልክተዋል።

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ  ስለ ህንፃ ግንባታ ሂደቱ ገለጻ ማድረጋቸውን ከአገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም