ቀጥታ፡

በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፡- በተወረወሩብን የዕንቅፋት ድንጋዮች ኢትዮጵያን ገንብተንበታል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ዐቅሟ ትልቅ፤ ጸጋዋ ብዙ፤ ዕድሏ ሰፊ፤ መሆኑን ዐውቀናል ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልክዕት ገልጸዋል።


 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን ነው ብለዋል።

ትውልድ ሲጠይቀው የኖረውን የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን እናደርገዋለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም