ቀጥታ፡

የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፦ በሩዋንዳ ኪጋሊ ሲካሄድ የቆየው 26ኛው የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት(EAPCCO) ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቋል።

የሩዋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤድዋርድ ንጌንቴሬ(ዶ/ር) በ24ኛው የኅብረቱ የሚኒስትሮች ካውንስል ጠቅላላ ስብሰባ ለይ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል።


 

የቀጣናው አባል ሀገራት የፖሊስ አዛዦች እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በካውንስሉ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦች በሚኒስትሮቹ የውሳኔ ሀሳብ ውስጥ ተካተው ፀድቀዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ ኢትዮጵያን ወክለው በጉባዔው ማጠቃለያ ላይ መሳተፋቸውን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም