ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ትሻለች - አምባሳደር ገነት ተሾመ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ገለጹ።

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ሀገራት ልዩ ልዑክ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሚካይል ቦግዳኖቭ ጋር ዛሬ በሞስኮው ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች የኢትዮጵያ እና የሩሲያን የሁለትዮሽ ግንኙነት አስመልክቶ መክረዋል።

አምባሳደር ገነት ለቦግዳኖቭ በወቅታዊ ቀጣናዊ እና የጋራ ትብብር ጉዳዮች ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ገነት የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ እንደሚገኝ እና ኢትዮጵያ በፖለቲካ እና ኢኮኖሚው መስክ ያላትን ትብብር ማጠናከር እንደምትሻ መግለጻቸውን በሞስኮው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ሀገራት ልዩ ልዑክ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሚካይል ቦግዳኖቭ በበኩላቸው የከፍተኛ አመራሮች የስራ ጉብኝት ልውውጦች ለሁለቱ ሀገራት ትብብር ማደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም