ቀጥታ፡

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በስድስት ወራት ውስጥ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2017(ኢዜአ|)፦ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር) የ2017 የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ በስድስት ወራት ውስጥ በሺፒንግ አገልግሎት ከሁለት ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነት በባህር ማጓጓዙን ገልጸዋል።

በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ከ654 ሺህ ቶን በላይ የገቢና ከ174 ሺህ ቶን በላይ የወጪ ዕቃዎች ማስተናገዱን ጠቁመዋል።

በዚህም በስድስት ወራት ውስጥ ከሌሎች የገቢ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።


 

ባለፉት ስድስት ወራት ኤክስፖርት ላይ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ጠቁመዋል።

በኮርፖሬት ስራዎችም ለረጅም ጊዜ ሳይዘጉ የቆዩ ሂሳቦችን መዝጋት መቻሉን ገልጸው፤ ያልተሰበሰቡ ሂሳቦችን ለመሰብሰብም የተሰራው ስራ ውጤት ማስገኘቱን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜ እየተጠናቀቁ ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቅሰው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም