የፌዴራል ፖሊስ ስዋት በዓለም አቀፉ ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ለመሳተፍ ልምምድ እያደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል ፖሊስ ስዋት በዓለም አቀፉ ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ለመሳተፍ ልምምድ እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን የተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች በምታስተናግደው የዓለም አቀፍ ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጅቱን በዱባይ እያደረገ ይገኛል።
ቡድኑ ልምምዱን እያደረገ የሚገኘው በዱባይ አልሩዋይ ከተማ በሚገኘው የ"SWAT Challenge" ማሰልጠኛ ማዕከል ነው።
በፈረንጆቹ ከየካቲት 1 እስከ 5 /2025 በሚካሔደው የፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ውድድር ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል የሚሳተፍ መሆኑንም ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።