የኢትዮጵያ ፖሊስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥና መንግስት ያቀዳቸው የልማት ስራዎች እንዲከወኑ ትልቅ ድርሻ አበርክቷል- ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፖሊስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥና መንግስት ያቀዳቸው የልማት ስራዎች እንዲከወኑ ትልቅ ድርሻ አበርክቷል- ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/ 2017 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ፖሊስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥና መንግስት ያቀዳቸው የልማት ስራዎች እንዲከወኑ ትልቅ ሚና መጫወቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለተቋሙ ስትራቴጂክ አመራሮች እና የፖሊስ መኮንኖች ባለፉት ስድስት ዓመታት በተቋሙ ሲተገበር የቆየው የለውጥ ሂደት ላይ ያዘጋጀው የውይይት መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ፥ በተጨባጭ የተገኙ የለውጥ ፍሬዎችን በተጠናከረ መልኩ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
አክለውም፥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል በሰጡት መመሪያ መሠረት ከስትራቴጂክ አመራሩ ጀምሮ እስከ ታችኛው የአመራር እርከን ያሉ እንዲሁም መላው ሠራዊት በለውጡ የተገኙትን ውጤቶች በትክክል ተረድቶ በቀጣይ ከእያንዳንዱ የፖሊስ አመራር እና አባል ምን እንደሚጠበቅ በሚገባ አውቀው ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑንም ገልፀዋል።
የተቋሙ አመራሮች እና ሰራዊቱ የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።