የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017(ኢዜአ)፦ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ የካቲት 1 እና 2 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ዋና ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ስለ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የፖሊሲ ጉዳዮች እና እየተደረጉ ባሉ ሪፎርሞች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ክሪስታሊና ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድ እና ኢኮኖሚ እድሎች አስመልክቶ ሀሳቦችን እንደሚለዋወጡም ገልጿል።
የዋና ዳይሬክተሯ ጉብኝት አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የፖሊሲ ምክክሮችን በማድረግ የማይበገር፣ የጋራ እና ዘላቂነት ያለው ብልጽግና እንደሚመጣ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት እንደሆነ ተመላክቷል።
ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እ.አ.አ በ2019 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ በመረጃው አስታውሷል።