ሪፎርሙ ለኢኮኖሚ መረጋጋትና እድገት ምቹ መደላድልን የሚፈጥር ነው- የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቢርድ - ኢዜአ አማርኛ
ሪፎርሙ ለኢኮኖሚ መረጋጋትና እድገት ምቹ መደላድልን የሚፈጥር ነው- የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቢርድ
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው ሪፎርም ለኢኮኖሚ መረጋጋት እና እድገት ምቹ መደላድልን እንደሚፈጥር የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አና ቢርድ ገለጹ።
ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ጋር በሪፎርሞቹ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በትግበራ ላይ የሚገኙት ወሳኝ ሪፎርሞች ለኢኮኖሚ መረጋጋት እና እድገት ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው አመልክተዋል።
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ሀገር መቀበል የሪፎርም አጀንዳ ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል ዳይሬክተሯ በመልዕክታቸው።