ምክር ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ጥር 22/ 2017 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።