የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል
አዲስ አበባ፤ ጥር 21/2017(ኢዜአ)፡- 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በ17ኛ መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።