ቀጥታ፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 21/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው 26ኛው የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት (EAPCCO) ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፋ ይገኛሉ።

ጉባዔው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቀጣናው ከሚገኙ የፖሊስ ተቋማት ጋር በትብብር ለመስራት ወሳኝ ዕድል እንደሚፈጥርለት ተገልጿል።


 

የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት በቀጣናው የሚገኙ የፖሊስ ተቋማትን በማስተሳሰር በጋራ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ መገለጹን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም