ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የቱሪዝም፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች በኦስትሪያው የአፍሪካ ቀን ሁነት ላይ ተዋወቀ

አዲስ አበባ፤ ጥር 20/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የቱሪዝም፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎቿን በኦስትሪያው ‘የአፍሪካ ቀን 2025’ ሁነት ላይ አስተዋወቀች።

በሀገረ ኦስትሪያ ርዕሰ መዲና ቪዬና በየዓመቱ የሚካሄደው የአፍሪካ ቀን የአፍሪካ ብዝሃ ባሕል፣ ምጣኔ ሀብታዊ ጸጋዎች የሚገለጥበትና የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የሚተዋወቁበት መድረክ ነው።

May be an image of 6 people and text that says 'MADIA MARIANA KÜHNEL Deputy Secretary DeputySecretaryGeneral General Austrian Federal Economic Chamber AFRICA BODOESSND DAY BE REA'

የኦስትሪያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በአፍሪካ ሀገራት የንግድ ስራና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር የሚያገለግል ሲሆን ዘንድሮ ለስምንተኛ ጊዜ በቬዬና ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።

በአካልና በበይነ መረብ ተሳታፊዎቹ በሚታደሙበት በዚህ ሁነት የአፍሪካ ሀገራት የኢንቨስትመንት ጸጋቸውን የሚያሳዩበትና አፍሪካም እንደ አህጉር ባህልና ኢኮኖሚያዊ መልኮቿ ለተቀረው ዓለም የሚገለጥበት አጋጣሚ ነው።

በዚህም በዘንድሮው በኦስትሪያ አፍሪካ ቀን መድረክ ላይ በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው ተሳትፈዋል።

አምባሳደሩ የቱሪስትና የኢንቨስተሮች መዳረሻ በሆነችው ኢትዮጵያ የሚገኙ መልከ ብዙ የቱሪዝም፣ የንግድን ኢንቨስትመንት ዕድሎችን አስተዋውቀዋል።

May be an image of 3 people and text

በሁነቱ የኢትዮጵያ የቡና ቅምሻ ስነ ስርዓት በመከወን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶችና ኢንቨስመንት ዕድሎችን በማስተሳሰር ለተሳታፊዎች መተዋወቁንም ጀኔቫ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል ።

May be an image of 1 person, table and text

የአፍሪካ ቀዳሚውና ምርጡ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁነቱ አዘጋጆች አጋር በመሆን በበይነ-አፍሪካ ትስስር የሚጫወተውን ቁልፍ ሚና አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም