ቀጥታ፡

አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 19/2017(ኢዜአ)፦ በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ፖዘቲቮ ቴክኖሎጂያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጆናታን ቢተንኮርት ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ልዑልሰገድ ከኩባንያው ኃላፊ ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎችንና ምቹ የንግድ ከባቢን አስመልክቶ ጠቃሚ እና ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ጋጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ እና የብራዚልን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መደረሱንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም