መንግስትና የህዝብን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
መንግስትና የህዝብን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመረቁ
ደሴ፤ ጥር 18 ቀን 2017 (ኢዜአ)፤ በአማራ ክልል መንግስትና የህዝብን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመረቁ።
የአማራ ክልል መንግስትና የህዝብን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተመርቀዋል፡፡
በምረቃ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደጀኔ ልመንህ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በማለም የሰላም ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
በተሃድሶ ቆይታቸውም ችግሮችን በሰላም የመፍታትና የክልሉን ህዝብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት እየሄደበት ያለውን ቁርጠኝነት ላይ ግንዛቤ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
በስልጠና ቆይታቸው በፈጸሙት ጥፋት ተጸጽተው ህዝባቸውን ለመካስና ለሰላም ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸው አረጋግጠናል ያሉት ምክትል ቢሮ ሃላፊው፤ ህብረተሰቡም ይቅርታቸውን በፍቅር ተቀብሎ ወደ ልማት እንዲገቡ የተለመደውን እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በሀገር መከላከያ ስራዊት የሰሜን ምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል በበኩላቸው፤ የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ላሳዩት መልካም ተግባር ምስጋና እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በበኩሉ፤ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በተለያዩ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡