ተቋማቱ ለውጭ ባለሀብቶች የተቀናጀ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ተቋማቱ ለውጭ ባለሀብቶች የተቀናጀ አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለውጭ ባለሀብቶች በቅንጅት አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።
የውጭ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ከሚገቡበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የቪዛ አገልግሎቶች እንዲሁም ለነባር ባለሀብቶች ቀልጣፋ፣ ምቹ እና የተሟላ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በተናበበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ሁለቱ ተቋማት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኮሚሽኑ ለውጭ ባለሀብቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የተለየ ዴስክ ለማቋቋም እና የተፋጠነ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ሌሎች እርምጃዎችን ለመውሰድ ተስማምተዋል።
በቀጣይም ተከታታይነት ያላቸው ውይይቶችን እንደሚያደርጉም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለውጭ ባለሀብቶች የተለያዩ አገልግሎቶች ከሚሰጡ የመንግስት ተቋማት በትብብር እንደሚሰራ ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።