በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ በህገወጥ የሰዎች እና በአደገኛ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ የምርመራ መዝገቦች እየተጣሩ ነው - ፌዴራል ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ በህገወጥ የሰዎች እና በአደገኛ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ላይ የምርመራ መዝገቦች እየተጣሩ ነው - ፌዴራል ፖሊስ
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፡- በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ በህገወጥ የሰዎች እና በአደገኛ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ በደረሰ ጉዳት የምርመራ መዝገቦች እየተጣሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የ2017 ዓ.ም የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ተቋማዊ ዕቅዱን ለማሳካት ሁሉንም አመራርና አባል በማሳተፍ የተሰጠውን ተልዕኮ ግብ ለማድረስ የፍትህ ስርዓቱን ታማኝና ግልፅ በማድረግ የተጀመሩ ውጤታማ የምርመራ ሥራዎችን በታክቲክ፣ በፎረንሲክና በድጋፍ ውጤት የተገኘባቸውን ስራዎች አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ብለዋል፡፡
የግማሽ በጀት አመቱ የተሻለ የመዝገብ አፈፃፀም የተመዘገበበት መሁኑን ገልፀው በተለይም በድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች በህገወጥ የሰዎችና፣ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር እንዲሁም በተለያዩ የኢኮኖሚ ወንጀሎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት ላይ በደረሰ ጉዳት የምርመራ መዝገቦች እየተጣሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የ2017 ዓ.ም የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል፡፡