ፋብሪካው የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያሻሻልና ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ፋብሪካው የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያሻሻልና ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፦ የኢቲ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያሻሻል እና የአካባቢውን ነዋሪ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የሚገኘውን ፋብሪካ ዛሬ መርቀው ስራ ማስጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ፋብሪካው በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የድንጋይ ከሰል ምርት ከማሻሻል ባሻገር ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን አመልክተዋል።