ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የአቪዬሺን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የአቪዬሺን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የአቪዬሺን ዘርፍ የሁለትዮሽ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጆን ዎጃ ኤሊናና ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት የአቪዬሽን ዘርፍ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
ሀገራቱ በአቪዬሽን መስክ በአቅም ግንባታና ልምድ ልውውጥን በማጠናከር በዘርፉ ያላቸውን አጋርነት ማጠናከር እንደሚቻል አንስተዋል።
አምባሳደር ነቢል ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን የአቪዬሺን ሪፎርም ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ተዓማኒና ዘላቂነት ያለው የአየር ትራንስፖርት ስርዓት ለመፍጠር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በጁባ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።