የወንጀል መከላከል አቅም ማጎልበቻ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢዜአ አማርኛ
የወንጀል መከላከል አቅም ማጎልበቻ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፦ የወንጀል መከላከል አቅምን ለማጎልበት የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማ እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የተያዘውን ሁሉን ባሳተፈ መልኩ ተቋማዊ ዕቅዱን ለማሳካትና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ እየተሰራ ነው።

ተቋማዊ ተልዕኮ ለማሳካትና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አሰራርን የበለጠ በማጠናከር የወንጀል መከላከል አቅምን ለማጎልበት የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመልክተዋል።
አያይዘውም በተቋሙ እየተተገበሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።