ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ቻይና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 16/2017(ኢዜአ)፦ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑካን ቡድን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቼን ዢያኦዶንግ ጋር ዛሬ በቤጂንግ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ በዋናነት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች እ.አ.አ 2023/24 ባደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ወቅት መግባባት ላይ የደረሱባቸው ጉዳዮች እና የተፈረሙ ስምምነቶች ትግበራ ላይ ያተኮረ ነው።


 

አቶ አሕመድ ሽዴ እና ሚስተር ቼን ዢያኦዶንግ የመሪዎቹ የስምምነት ነጥቦች እና የተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መተግበር ወሳኝ መሆኑን መግለጻቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

እ.አ.አ በ2024 ሀገራቱ በመሰረተ ልማት፣ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ እና በሌሎች መስኮች ያላቸውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር ትግበራ ማፋጠን እንደሚገባ አንስተዋል።

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም