አየር መንገዱ የቦይንግ 777F ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ የቦይንግ 777F ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ተረከበ
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 777F ዕቃ ጫኝ አውሮፕላን ዛሬ ተረክቧል።
አየር መንገዱ የካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዛሬ የተረከበው የቦይንግ 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላንም የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት አድማስ ለማስፋት እና እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ አስተዋፅጽኦ እንዳለው አመልክቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የላቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አጠናክሮ ቀጥሏል።
አዲሱ የካርጎ አውሮፕላንም ኩባንያው ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን እንደሚያግዙም ነው የገለጸው።
በተጨማሪም አውሮፕላኑ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ይዞ መምጣቱን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።