ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል
አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2017(ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያካሂደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህም የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጆች የተመራላቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የሚያቀርቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያደምጥም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም እጩ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ ምክትል ዕምባ ጠባቂ እና የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።