ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ሂደቱን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 14/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን የኢነርጂ እና ግድቦች ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሐፊ ሱልጣን ላም ቱንግዋር ኩዬግዎንግ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ነቢል በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የኃይል መስመር በመዘርጋት የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ሂደት ጥረቶችን ይበልጥ ለማፈጠን ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኃይል ትስስሩ ሀገራቱ እ.አ.አ በ2022 የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት አካል መሆኑንም ጨምረው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም