ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ሶስት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ ጥር 14/2017(ኢዜአ):- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያዳምጣል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም እጩ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ ምክትል ዕምባ ጠባቂ እና የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጆች የተመራላቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የሚያቀርቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም