አዲሱ የግብርናና የገጠር ልማት ፖሊሲ የትውውቅ መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አዲሱ የግብርናና የገጠር ልማት ፖሊሲ የትውውቅ መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
አሶሳ፤ ጥር 14/2017(ኢዜአ)፦ የግብርና ሚኒስቴር አዲሱ የግብርናና የገጠር ልማት ፖሊሲ የትውውቅ መድረክ በአሶሳ ከተማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ግብርናና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈጻሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር)፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተደድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፤ የሚኒስቴሩ እና የግብርናና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራር አባላት እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ፖሊሲው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃን ማሻሻል ዓላማ ያለው መሆኑ ታውቋል።