ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017 (ኢዜአ):- በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር(ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አምባሳደር ሳቀር አል ኩራሺ ጋር ዛሬ በሪያድ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትጫወተውን አዎንታዊ ሚና እና ተፅዕኖ ፈጣሪነት ያነሱ ሲሆን በዚህ ረገድም አገራቱ በቀጣናው ሰላምና ደህንነት ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ አገራት ካላቸው መልክዐ ምድራዊ ቀረቤታ፣ ማህበራዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አኳያ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ግንኙነቶቹን ይበልጥ ለማጠናከር የሚቻልባቸው ሰፊ አማራጮች ለመጠቀም እንደሚሰሩ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም