ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተርኪዬ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ጥር 15/2017 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተርኪዬ ቦሎ ግዛት በሆቴል ላይ በተነሳ እሳት ምክንያት ለደረሰው ሰብዓዊ ጉዳት ጥልቅ ሀዘኑን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በአደጋው ምክንያት የቅርብ ወዳጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ልባዊ መጽናናትን፣ በአደጋው ምክንያት የተጎዱ ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ተመኝቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ያለውን አጋርነት አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም