ቀጥታ፡

አምባሳደሮቹ የሀገራቱን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፡- በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ እና በጀርመን የሊሽተንስታይን አምባሳደር ኢዛቤል ፍሮሜልት-ጎትሻልድ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያና ሊሽተንስታይን በንግድና ኢንቨስትመንት በንግድ እንዲሁም በባለብዝሃ ወገን የትብብር አማራጮች ላይ ግንኙነትን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በመካከለኛው አውሮፓ የምትገኘው ሀገረ ሊሽተንስታይን በጀርመን በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሚሸፍናቸው አገራት መካከል አንዷ ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም