ቀጥታ፡

ዩኒቨርሲቲ በዕውቀት መር የማህበረሰብ አገልግሎትን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

ጋምቤላ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ከሰው ኃይል ልማት ማፍራት ባሻገር ዕውቀት መር የማህበረሰብ አገልግሎትን አጠናክሮ እንዲቀጥል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ዑሞድ ጠየቁ።

ዩኒቨርስቲው ስድስት የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ይፋ አድርግል።

በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚተገበሩት ፕሮጀክቶቹ በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም መስኮች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።

ርዕሰ መስተዳድሯ ወይዘሮ አለሚቱ ዑሞድ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ በማህበረሰብ አገልግሎት የጀመረውን ጥረት አድንቀዋል።

በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ዕውቀት መር የማህበረሰብ አገልግሎትን በማጠናከር የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እንዲግዝ ጠይቀዋል።


 

የክልሉ መንግስት  ለፕሮጀክቶች ስኬታማነትም ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮ የመማር መስተማር፤ የምርምርና እውቀት መር የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ነው ብለዋል፡፡


 

በዚህም ዩኒቨረስቲው  የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሻሉ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዕለቱ ይፋ የሆኑ ስድስት ችግር ፈቺ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችም በራሱ በጀት  የሚተገበሩ ናቸው ብለዋል።

የውሃ፣ የማንጎ ምርት ማሻሻያ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ ማስፋፋና የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ከፕሮጀክቶቹ መካከል ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም