የኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ከየካቲት 5 ጀምሮ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር መርሃ ግብር ከየካቲት 5 ጀምሮ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሶስተኛ ዙር ጨዋታዎች የሚካሄዱባቸው ቀናቶች ይፋ ሆነዋል።
መርሃ ግብሩ ከየካቲት 5 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እና በሃዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ሐረር ከተማ ከሀዲያ ሆሳዕና፣ ስሑል ሽሬ ከሲዳማ ቡና፣ ነገሌ አርሲ ከሃዋሳ ከተማ፣ ባህር ዳር ከተማ ከሃላባ ከተማ፣ መቻል ከሱሉልታ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማ ከወላይታ ድቻ፣ ሸገር ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣይ ዓመት በሚካሄደው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።
በ1937 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 80 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።