ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ጋር ያላት የጸና ትብብር ለጋራ ዕድገት ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነው-ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ጥር13/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ጋር ያላት የጸና ትብብርና የመሠረተ ልማት ትስስር ለጋራ ዕድገትና ለአዳዲስ ዕድሎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነው ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ፥ ዛሬ በኢትዮ-ሎጅስቲክስ የዘርፍ ማኅበራት በተዘጋጀው የቢዝነስ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተዋል።

በዚህም ከጂቡቲ ጋር ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት አስፈላጊነት እና የኢትዮጵያ መንግስት በቀጣናው የንግድ እድሎችን ለማሳደግ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ብለዋል።

ከጂቡቲ ጋር ያለን የጸና ትብብርና የመሠረተ ልማት ትስስር ለጋራ ዕድገትና ለአዳዲስ ዕድሎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ተግዳሮቶችን በማስወገድ ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ስምምነት ጋር የሚስማማና አስተማማኝ የትብብር ማዕቀፍን እውን ለማድረግ በትጋት እየሰራ ነው መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግና ግብርናን መሰረት ያደረገና ብዝሃነት ያለውን የውጭ ንግድ ለማስፋት ለሚሰራው ስራ ጂቡቲ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም