የሃጅ ጉዞ ምዝገባ  የፊታችን ሐሙስ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ የዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ምዝገባ ከጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለጸ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ሃጅ ካሚል ሀሩን በሰጡት መግለጫ ምዝገባው የካቲት 21 ቀን 2017 ይጠናቀቃል ብለዋል።

ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 30 የምዝገባ ጣቢያዎቹ የሚካሄድ ሲሆን መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ በቀነ ገደቡ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ተጓዦች ለምዝገባ ሲመጡ የቀበሌ መታወቂያና የታደሠ ፓስፖርት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል። 

በዘንድሮው የሃጅ ጉዞ ለ10 ሺህ ተጓዦች መፈቀዱንም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም