ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በፍትህ ዘርፍ ባላቸው ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጂቡቲ የፍትህ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ባህዶን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ በማህበረሰቡ ላይ ችግር እያስከተሉ ያሉ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

በተጨማሪም በሲቪል እና በንግድ ስርዓት፣ በህግ ዘርፍ የሁለትዮሽ ትብብርን ማሳደግ፣ መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥ እና በፍትህ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም