ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ጀርመን በኢኮኖሚና የልማት ትብብራቸው ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ቢርጊት ፒኬል ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ እና ጀርመን የኢኮኖሚ እና የልማት የሁለትዮሽ ትብብር ላይ ያተኮረ ነው።

በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተተገበሩ ባሉ የሪፎርም እርምጃዎች ላይ ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም