በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በቻይና ጉብኝት እያደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በቻይና ጉብኝት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቻይና ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ልዑኩ ከቻይና ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ እና ንግድ ባንክ፣ ከቻይና ልማት ባንክ፣ ከቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ እና ከቻይና ኤግዚም ባንክ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ምጣኔ ሀብታዊ ትብብርን ለማሳደግ እንደሚሰራ ተገልጿል።
አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና እድሎችን በተመለከተ ለቻይና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።