ቀጥታ፡

የጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው ተጠናቀዋል-የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል

አዲስ አበባ፣ጥር 12/ 2017 (ኢዜአ)፦ የጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ሃይሉ አስታውቋል።

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ጨምሮ ገልጿል።

በመሆኑንም በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት እና ለበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የፀጥታ ተቋማት አመራርና አባላት የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ምስጋና ማቅረቡን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም