ቀጥታ፡

የኮትዲቭዋር የመንግስት ልዑክ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሰራርና አደረጃጀት ላይ ከኢትዮጵያ የልምድ ልውውጥ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ የኮትዲቭዋር የመንግስት ልዑካን በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አሰራርና አደረጃጀት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ የኮትዲቭዋር መንግስት ልዑካን ቡድንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ልዑኩ በቀጣይ ቀናት የአግሮ እንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚጎበኝም ተገልጿል።

የልዑኩ ጉብኝት አላማ በኢትዮጵያ ያሉ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አሰራርና አደረጃጀት አስመልክቶ ተሞክሮ ለመቅሰም እንደሆነ ተገልጿል።

አቶ ሀሰን የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አደረጃጀትና አሰራር፣ የወጪ ንግድ ድርሻ፣ የስራ እድል ፈጠራ አበርክቶ እና ተጓዳኝ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለልዑኩ ገለጻ አድርገዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያና ኮትዲቭዋር በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያደርጉት የልምድ ልውውጥ ለሁለቱም ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግርና ቀጣይነት ላለው ዕድገት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል።

የኮትዲቭዋር መንግስት ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን አደረጃጀትና አሰራር ማድነቁን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም