ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ከከምባታ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር በሠላም፣ በአብሮነትና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ከከምባታ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር በሠላም፣ በአብሮነትና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
ሆሳዕና፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)፣ ከከምባታ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር በዞኑ ሠላምን፣ አብሮነትንና ልማትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
መድረኩ የሕዝቦችን አብሮነትና አንድነት በማጠናከር የልማትና የመልካም አስተዳደር ግንባታን ለማፋጠን የሚያግዝ መሆኑንም ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ርዕሰ መስተዳድሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ምስጋና ማቅረባቸው በመረጃው ተመላክቷል።