ቀጥታ፡

የጥምቀት በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ጥር 11/2017(ኢዜአ)፦የጥምቀት በዓል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ በጃንሜዳ፣ በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በጋምቤላ፣ በባቱ እና በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ነው፡፡


 

ትናንት የከተራ በዓል በመላ ሀገሪቱ የተከበረ ሲሆን በዚህም በሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት መሰረት ታቦታት ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ ጥምቀት ገብተዋል።

በዛሬው ዕለትም በባህረ ጥምቀት ስፍራ የተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከናወነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም