በደምበል ሐይቅ የከተራ ክዋኔ የተደነቁት የባሕር ማዶ ቱሪስቶች - ኢዜአ አማርኛ
በደምበል ሐይቅ የከተራ ክዋኔ የተደነቁት የባሕር ማዶ ቱሪስቶች

አዲስ አበባ፤ ጥር 10/2017(ኢዜአ)፦ በባቱ ደምበል ሃይቅ ላይ በተከናወነው የከተራ በዓል አከባበር በእጅጉ መደነቃቸውን የተለያዩ የውጭ አገራት ቱሪስቶች ተናገሩ ።
የከተራ በዓል በባቱ ደምበል ሀይቅ የኃይማኖት አባቶች፣ በርካታ ምእመናን፣ የውጭና የሃገር ውስጥ ቱሪስቶች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርአት ተከብሯ።
ከተለያዩ አገራት በመምጣት በክብረ በዓሉ ላይ ከተገኙት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ቱሪስቶች በባቱ ደምበል ሀይቅ ላይ በተከናወነው የከተራ በዓል አከባበር በእጅጉ መደነቃቸውን ገልጸዋል።
የበአሉ አከባበር የተለየ ትእይንት ያለው የሚያምርና ደማቅ ስነ ስርአት ያለው በመሆኑ ከየትኛውም አገር አከባበር የተለየ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።
በዚህ ክብረ በዓል ላይ በመገኘታችን እድለኞች ነን በእጅጉም ተደስተናል ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሚከናወነውን የከተራና የጥምቀት በዓል ሁሉም መጥቶ ቢጎበኘው የሚደሰትበት ይሆናልም ነው ያሉት።
ከአዲስ አበባ እና ሌሎች አካባቢዎችም የታደሙ እንግዶችም በደምበል ሃይቅ የነበረው የከተራ በዓል አከባበር እና የጀልባ ትርሂት አስደሳችና ማራኪ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተራ በዓል ደምበል ሀይቅ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት በጀልባ እና ታንኳ ትርኢት ታጅቦ በደማቅ ስነ ስርአት የተከናወነ ሲሆን የጥምቀት በዓልም በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።